ስንቅ

Published on February 01, 2020 by Zetseat Church, Kaleab S. Melkie

በማኅበራዊ ሥነ-ልቦና ውስጥ ለመንጋ አስተሳሰብ በርካታ ማብራሪያዎች አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ: ከራስ ጋራ መለያየት (Deindividuation)፤ ይህ ማለት ግለሰቦች በመንጋው ውስጥ ማንነታቸውን ሲያጡና ራሳቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው ነው። ሌላው ማኅበራዊ ተፅዕኖ (Social Influence) ሲሆን ሰዎች የቡድኑን አባላት ፍላጎትና እምነት ለማርካት ሲሉ የራሳቸውን እምነትና አቋም ወደ ጎን በመተው መንጋውን ሲከተሉ ነው። ለመንጋው አስተሳሰብ መፈጠር በምክንያትነት የሚጠቀሰው ሌላው ነጥብ ፍርሃት ሲሆን ይህም ግለሰቦች ከመንጋው በተለየ መንገድ ካሰቡና ከተንቀሳቀሱ ሊደርስባቸው የሚችለውን መገለል በመፍራት የሚከተሉት መንገድ ነው።

እግዚአብሔር ግን እያንዳንዳችንን የፈጠረን በተለየ ማንነትና ለተለየ ዓላማ ነው። ስለዚህ የመንጋውን ድምፅ በጭፍን በመከተል የራሳችንን መለኮታዊ ጥሪና ማንነት ማጣት የለብንም። ቃሉ እንዲህ ይላል: “ዘመኑን ለመዋጀት ጥበብ ይኑራችሁ”። ዛሬ ቆም ብለን የምንሰማውንና የምንከተለውን መንገድ እንመርምር።

subscribe

Register your email with us to receive updates.